ነሐሴ 16, 2023
ውድ የRainier Beach መኖሪ መንደር ነዋሪዎች:
ኤምቲ. ቤከር የመኖሪ ቤት ማህበር (Mt. Baker Housing Association, MBH) በ2021 ላይ 53,000 SF ቦታ በ4215 S. Trenton Street ከRainier Beach የቀላል ባቡር ጣቢያ ባሻገር ከሲያትል የቤቶች ቢሮ እና ከዋሽንግተን የቤቶች ፋይናንስ ኮሚሽን የመሬት ማግኛ ፕሮግራም በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ገዝቷል። MBH በቅርቡ ትይዩ የሆነ የንድፍ ሂደትን ከTubman Health and Freedom ማዕከል ጋር በመተባበር ከአንድ የማህበረሰብ ጤና ጣቢያ አጠገብ ተመጣጣኝ የሆነ የባለብዙ ቤተሰብ አፓርትመንት ህንጻ ለማቅረብ ሂደቱን ጀምሯል።
MBH የአካባቢውን ከ50% እስከ 60% መካከለኛ ገቢ እና ከዚ በታች ለሚያገኙ ቤተሰቦች የተዘጋጁ ቢያንስ 281 መኝታ ክፍሎችን የሚይዙ 170+ ክፍሎች ያሉት የአፓርታማ ህንጻ ይገነባል። MBH በዲዛይኖቹ ላይ ቢያንስ 40% ያክሉን ክፍሎች ባለ ሁለት እና ሶስት መኝታ ክፍሎች በማድረግ እና ለሁሉም ቤተሰቦች የሳይት ላይ ተደራሽ የሆኑ የቤት ውስጥና ከቤት ውጭ መገልገያዎችን በማዘጋጀት ለትልልቅ የብዙ ትውልድ ቤተሰቦች ፍላጎቶች ቅድሚያ እየሰጠ ነው። የአሁኑ ፕላን የትላልቅ ቤተሰቦችን የትራንስፖርት ፍላጎት የማስተናገድ ግብ ያለው ከመሬት በታች የመኪና ማቆሚያን ያካትታል። MBH ነዋሪዎችን እና የመኖሪ መንደሮችን በTubman Health አማካኝነት ከሚቀርቡ የጤና እንክብካቤዎችና የጤናማነት ፕሮግራሞች ጋር የማገናኘት ፍላጎት አለው።
ለጤና ማዕከሉ ክፍል ለመስጠጥ MBH ለ125′ ቁመት በተዘጋጀው የቦታው ክፍል ላይ ባለ 12 ፎቅ አፓርትመንት ሕንፃ ይገነባል። Tubman Health ለ55′ የተከለለውን የጣቢያው ምዕራባዊ ጎን የተወሰነውን ክፍል የሚገዛ ሲሆን ነጻ ባለ ሶስት ፎቅ በጥቁር ማህበረሰብ በባለቤትነት የሚመራ እና የሚተዳደር የጤና እንክብካቤ አገልግሎት እና የሰው ሃይል ልማት ከመሬት በታች የመኪና ማቆሚያ ጋር ለመገንባት አእቅድ ተይዟል። የTubman Health ግንባታ በ2024 ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ከአፓርታማ ህንጻው ተለይቶ ዲዛይን የሚዘጋጅለት፣ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግለት እና የሚሰራ ይሆናል። MBH የአፓርታማ ህንጻውን ግንባታ በ2025 መጨረሻ ላይ ለመጀመር አቅዷል። መረጃ ከሲያትል አገልግሎቶች ፖርታል (Seattle Services Portal): https://cosaccela.seattle.gov ላይ መዝገብ: 3039497-LU ላይ ፈልጎ ማግኘት ይቻላል።
እባክዎ ስለ ፕሮጀክቱ መረጃ ለመስማት እና በአፓርታማ ህንጻው ዲዛይን ላይ ግብዓትዎን ለማጋራት በቀጣዩ በRainier Beach Public Library በሚካሄደው ስብሰባችን ላይ ይቀላቀሉን።
የስብሰባ ቀን: | የስብሰባ ሰዓት: | በota: |
ሀሙስ፣ ነሀሴ 31, 2023 | 2:00-3:30pm | Rainier Beach Public Library |
ሀሙስ፣ ነሀሴ 31, 2023 | 6:00-7:30pm | 9125 Rainier Ave. S. |
ቀedamy, msekrme 23, 2023 | 12:30-2:00pm | Seattle, WA 98118 |
ይህን ፕሮጀክት ስኬታማ ለማድረግ ጥያቄዎችዎን፣ አስተያየቶችዎን እና ሀሳቦችዎን መስማት እንፈልጋለን።
ድረገጻችንን በ፡ https://mtbakerhousing.org/comment_forms/trenton-english/ ይጎብኙ።
QR ኮዱን ስካን በማድረግ ወይም ከታች የተገለጸውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኦንላይን የቤት ዳሰሳ ጥናት መሙላት ይችላሉ።
https://forms.office.com/r/qSXv0epvUF
ማንኛውም ጥያቄዎች ካሉዎ እባከዎ የMt. Baker Housing Association ከፍተኛ የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ የሆኑትን Alisha Dall’Ostoን በ፡ [email protected]. ያነጋግሩ።
እናመሰግንዎታለን
Mt. Baker Housing Association
Submit Community Feedback